ባህርዳር ከነማ ቀጣይ አመት ስብስባቸዉን ለማጠናከር በማሰብ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ ይገኛሉ።
የጣና ሞገዶቹ አይቬሪኮስታዊዉን ኢንተርናሽናል አብዱላዚዝ ሲአሆኔን ማስፈረማቸዉን ይፋ አድርገዋል፤ 1.82 ሜትር የሚዝመዉ ይህ ተጫዋች ሀገሩን በቻን ዉድድር በመወከል ያገለገለ ሲሆን በአይቮሪኮስት ወጣቶች ቡድንም መጫወት ችሏል።
ከ 2016 እስከ 2023 ለ አራት ክለቦች ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ አይቬሪኮስታዊዉ ተጫዋች ለባህርዳር ከነማ የሁለት አመት ኮንትራት ፈርሟል።