አሰልጣኝ በረከት ደሙን የክለባቸዉ ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ የሾሙት የ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆኑት አርባምንጭ ከተማዎች የአራተኛ ተጫዋቻቸዉን ዉል ሲያድሱ አንድ ተጫዋች ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
በትላንትናው እለት የሶስት ተጫዋቾችን ዉል ያደሱት አዞዎቹ በዛሬው እለት የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነዉን የበላይ ገዛኸኝን ኮንትራት በሁለት አመት ዉል ያደሱ ሲሆን እንዲሁም የቀድሞዉን የፌዴራል ፖሊስ የመስመር አጥቂ የሆነዉን ተመስገን መንገሻን በሁለት አመት ኮንትራት ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
ክለቡ በቀጣይ ቀናትም የሌሎች ተጫዋቾችን ዉል እንደሚያድስ እና ወደ ስብስቡ አዳዲስ ተጫዋቾችን እንደሚቀላቅል ለማወቅ ችለናል።