በሊጉ የ24ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ቀዳሚ መርሀግብር አርባምንጭ ከተማን ከወላይታ ድቻ አገናኝቶ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል ።
በጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ በኩል በ23ኛው ሳምንት በፋሲል ከነማ በተረተቡት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦችን ሲያደርጉ በአበበ ጥላሁን ፣ ወርቅይታደስ አበበ እና ኤሪክ ካፓይቶ ምትክ አካሉ አትሞ ፣ ቡታቃ ሸመና እና አህመድ ሁሴንና ጨዋታውን ጀምረዋል ። በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ በሳምንቱ ከአዳማ ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ አስራ አንድ ሁለት ለውጦችን በማድረግ ያሬድ ዳዊትን እና ቢኒያም ፍቅሬን በደጉ ደበበ እና ስንታየሁ መንግስቱ ተክተው ገብተዋል ።
ቀዝቀዝ ያለ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በታየበት እና በሙከራ ደረጃ ያን ያህል ጠንከር ያለ ሙከራ ባልያተየበት የመጀመሪያው አጋማሽ አርባምንጭ ከተማ በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ የተሻሉ ነበሩ ።
- ማሰታውቂያ -
አዞዎቹ ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት በተለይም ከፊት መስመር በሚገኙት አህመድ ሁሴን እና ተመስገን ደረሰ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን አድርገዋል ።
በራሳቸው ሜዳ ላይ በቁጥር በርከት ብለው አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ያሳለፉት ወላይታ ድቻዎች አርባምንጭ ከተማች የግብ ሙከራዎችን አንዳያደርጉ በማድረግ በእግራቸው ስር የሚቡበ ኳሶችን ደግሞ በረጅም ወደ ፊት በመላክ የተወሰኑ የማጥቃት አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ጥረቶችን አድርገዋል ።
በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በጦና ንቦቹ በኩል ስንታየሁ መንግስቱን ቀይረው በማስገባት የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ለማጠናከር ሞክረዋል ።
በዚህኛውም አጋማሽ አዞዎቹ የተሻሉ ነበሩ ። ወደ ግብ በመቅረቅ ረገድ ራሳቸው ከነበራቸው የመጀመሪያ አጋማሽ እንቅስቃሴም አንፃር የተሻሉ ደቂቃዎችን አሳልፈዋል ።
ነገር ግን የአርባምንጭ የማጥቃት ሂደት ወደ ግብ ደርሶ ዕድሎችን የፈጠረ ቢንያም ገነቱንም የፈተነ አልነበረም ።
በመጨረሻም ጨዋታው ያለግብ አቻ ተጠናቋል ።
በ25ኛው ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ግንቦት 12(ቅዳሜ) ከ9:00 ጀምሮ አዳማ ከተማ አርባምንጭ ከተማን ሲገጥም በተከታዩ ቀን ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታል ።