የድሬዳዋ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች የሆነው ያሬድ ዘውድነህ በአውሮፓ የሙከራ እድል አግኝቷል ።
በ2011 የውድድር አጋማሽ የትውልድ ከተማው የሆነውን ድሬዳዋ ከተማ ለመጫወት ፊርማውን ያኖረው ተጫዋቹ በአውሮፓ የሚገኘው የማክዶንያ ሐገር ክለብ የሆነው ሲሌክስ እግር ኳስ ክለብ የሁለት ሳምንት የሙከራ እድል አግኝቷል። በአውሮፓ ለሚኖረው ቆይታ ክለቡ ሲሌክስ ሙሉ ወጪውን እንደሚሸፍን የድሬዳዋ ስፖርት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል።