በሁለተኛው ዙር የእሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ዮሐንስ ሳህሌን የቀጠሩት ወልዋሎዎች ከሁለተኛው (ወልዋሎ ቢ) ቡድናቸው ሁለት ተጨዋቾችን እሳድገዋል።
በግማሽ ዓመት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ እንድ ተጨዋች ብቻ ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ግብ ጠባቂ ሽሻይ መዝገቦና የመስመር እጥቂው ስምዖን ማሩ ወደ ዋናው ቡድን እሳድጓል።
የመስመር እጥቂው ስምኦን ማሩ እምና ከ17 ዓመት የእዲግራት ቡድን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን በተመሳሳይ ከወልዋሎ ሁለተኛ ቡድንም የተሳካ ጊዜያትን እሳልፏል።ግብ ጠባቂው ሽሻይ መዝገቦም በተመሳሳይ ከሁለተኛው ቡድን ጋር ጥሩ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ሲሆን በቅርቡ ከክለቡ ጋር የተለያየውን ዮውሃንስ ሽክሩን ይተካል ተብሎ ይጠበቃል።