በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የማሊውን ክለብ ስታድ ማሊያን በደርሶ መልስ ጨዋታ በድምር ሁለት ለአንድ አሸንፎ ያለፈው ሆሮያ ኤፍ ሲ ለማጣሪያው ሁለተኛ ጨዋታ ዢ ኤስ ካቢሊን ይገጥማል። የመጀመሪያው ጨዋታም ከመስከረም 3 እስከ 5 ባሉት ቀናት ውስጥ ይደረጋል።
የቀድሞው የቡና አለቃ በሩዋንዳ ፖሊስ የአፍሪካ ሥራቸውን ቢጀምሩም በካሜሩን ኮተን ስፖርት ሰርተው የተጓዙት ወደ አልጄሪያው ኮንስታንቱን ነበር። በአልጄሪያ ኮንስታንቲንና ስኪክዳን ያሰለጠኑት ጎሜስ አሁን ደግሞ የጊኒውን ሆሮያን እየመሩ ካቢሊን ይገጥማሉ።
- ማሰታውቂያ -
ዢ ኤስ ካቢሊ የሱዳኑን አልሜሪክን ገጥሞ በአልጀርስ 1-0 በማሸነፍ በካርቱም ደግሞ 3-2ተሸንፎ በድምር 3-3ነገር ግን ከሜዳ ውጭ በገባ 2 ጎል ሁለት ጎል ታግዞ ነው ሆሮያን የሚገጥመው። የሆሮያና የዢ ኤስ ካቢሊ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር በአልጀርስ የመልስ ጨዋታው ደግሞ በኮናክሪ ይደረጋል።