ለ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን የማጣሪያ ጨዋታቸዉን እያከናወኑ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛዉ ዙር የመልስ ጨዋታ ናይጀሪያን ለመግጠም ወደ አቡጃ በትላንትናው ዕለት ያመሩ ሲሆን ነገር ግን በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እንግልት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
በዚህም ከ4:40 ደቂቃ በረራ በኋላ ከአዲስ አበባ አቡጃ ናምዲ አዚክዌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የደረሱት ሉሲዎቹ ከትኬት እና ቪዛ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በኤርፖርቱ ውስጥ ለአምስት ሰአታት ያህል እንግልት እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ተችሏል። ሆኖም ግን ከዚያም በኋላ በትላንትናው ዕለት ሉሲዎቹ መጠነኛ ልምምድ ማድረጋቸዉ ታውቋል።
እንደሚታወቀው የሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያ ጨዋታ አዲስአበባ አበበ ብቂላ ላይ አንድ አቻ መጠናቀቁ ይታወቃል።