የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የጦና ንቦች የቀድሞ የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ የነበሩትን ያሬድ ገመቹን የክለባቸዉ ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ ሾመዋል።
ክለቡ ከቀድሞ አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ጋር ያለዉ ዉል በመጠናቀቁ የተለያዩ ሲሆን በእሱም ምትክ አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ በሁለት አመት ኮንትራት ክለቡን እንዲያሰለጥን የክለቡ ቦርድ ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ ወስኖ አሰልጣኙን ሾሟል።