በሞሮኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር መስከረም 12 ቀን 2015 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያከናውናል፡፡ ለዚህ የማጣርያ ጨዋታ አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ እና ረዳቶቻቸው ለ36 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከነሐሴ 24 ጀምሮ በካፍ ልህቀት ማዕከል ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ተጫዋቾች ቡድኑን ያልተቀላቀሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከኢትዮጵያ ቡና የተመረጡት ተጫዋቾች ይጠቀሳሉ። በመሆኑም ለውድድሩ የቀረው ጊዜ አጭር ከመሆኑ አንፃር ከተመረጡት ስድስት ተጫዋቾች መካከች ኃይለሚካኤል አደፍርስ ፣ ጫላ ተሺታ ፣ ብሩክ በየነ እና መሐመድ ኑር ናስር ቡድኑን እንዲቀላቀሉ በድጋሚ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ሌላው የክለቡ ተጫዋች አማኑኤል ዮሐንስ በአዲስ መልክ ጥሪ የቀረበለት ተጫዋች ሆኗል።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የወላይታ ድቻ የተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ሳሙኤል ተስፋዬ ጥሪ ቀርቦለታል።

- ማሰታውቂያ -

ብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከመቻል ስፖርት ክለብ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርጓል።