በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ ለአዲሱ የውድድር ዘመን እና ለሁለተኛዉ ዙር የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማገባደድ ችሏል።
በዚህም የተጠናቀቀዉን የውድድር አመት በአርባምንጭ ከተማ ቤት ማሰለፍ የቻለዉ ተከላካዩ አሸናፊ ፊዳ እና በተመሳሳይም ከዚህ ቀደም ለጋሞ ጨንቻ መጫወት የቻለዉ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት አመታት ደግሞ በአዞዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ አማካዩ እንዳልካቸዉ መስፍን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ለፈረሰኞቹ ለመጫወት ፊርማቸውን ማኖራቸዉ ታውቋል።