ሃይላንድ ውሃን የሚያመርተው አስኩ የታሸገ ውሃ አምራች ኩባንያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እስከ አመቱ መጨረሻ የሚቆይ ስምምነት ተፈራረሙ።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር መዝናኛ ክበብ ውስጥ በተካሄደ የውል ስምምነት መሰረት ስምምነቱ በአይነት መሆኑ ተገልጿል። የክለቡ ዋና ጸሃፊ አቶ ንዋይ በየነ ሲናገሩ ” ከተቋሙ ጋር ያለን ስምምነት እስከ አመቱ መጨረሻ የሚቀጥልና በየአመቱ የሚታደስ ሆኖ በአይነት ነው በክለባችን ትልቁ ወጪ ከተጨዋቾች ደመወዝ፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴልና አራተኛ የውሃ አቅርቦት ሲሆን የሁሉሞ ቡድኖቻችን የውሃ አቅርቦት የሚሸፍን ስምምነት ነው” ሲሉ ተናግረዋል። “በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት እግር ኳስ ሜዳ ላይ በፌስቡክ በቴሌግራም ገጾቻችን የህ ትመት ውጤቶች ቢሾፍቱ የሚገኘው የክለባችን የመለማመጃ ሜዳ ላይ የተቋሙን ምልክት ማድረግ የቲቪና የቢልቦርድ ማስታወቂያ ላይ የክለባችን ተጨዋቾች የተቋሙን ውሃ እንዲያስተዋውቁ ማድረግን ያካትታል” ሲል አቶ ንዋይ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ንዋይ መግለጫ ” የሀገሪቱ ኡኮኖሚ አስቸጋሪ በሆነበት ሂደት አብረውን ለመስራት የፈለጉ እንደ ሃይላንድ ያሉ ተቋማት በመገኘታቸው ደስ ይለናል ከግል ኩባንያዎች ጋር ለመስሬት በመቻላችን ተደስተናል የውሃ ወጪያችንን ለማስወገድ ከአስኩ ኩባንያ ጋር ያደረግነው ስምምነት ይጠቅመናል ስምምነቱ የአንድ ወገን ጥቅም ሳይሆን ሁለታችንም ተጠቃቅመን አብረን የምንሄድበት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ” ሲሉ አስረድተዋል።
የአስኩ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው በበኩላቸው “ይሄ ስምምነታችን ለኩባንያችን ትልቁ ስኬት ነው ታላቅም ኩራት ነው በስፖርት አለም ቀዳሚ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስና በታሸገ ውሃ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሆነው ድርጅታችን መሃል የተፈጠረው ጥምረት ትልቅ ደስታን የፈጠረ ነው ድርጅታችን ከ60ሺህ በላይ ውሃዎችን ለገበያ የማቅረብ አቅም ያለው ነው ይህን በማድረጋችን ደስተኞች ነን ከ600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ ዕድል መፍጠራችንም ያስደስተናል ለፈጠርነው ግንኙነት ክለቡን አመሰግናለሁ” በማለት ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው ” በስፖርቱ ውስጥ በ87 የድል አመታት ያሸበረቀ ክለብ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስና በታሸገ ውሃ ኢንዱስትሪው ፈር ቀዳጅ በሆነው ሃይላንድ ውሃ ስም የተፈጠረው ስምምነት እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ነው ሃይላንድ ውሃ በታላቅ ጥረት ታላቅ ስኬት ጋር እንደሚደርስ እናምናለን” ሲሉ ተናግረዋል።