👉..መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ዳግም ይመረጡ ይሆን ..?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት አክሲዮን ማህበሩን በቦርድ ፕሬዝዳንትና አመራርነት የሚመሩ ሰባት አመራሮችን ነገ ይመርጣል።
ነገ ጠዋት በካፒታል ሆቴል በሚደረገውና የ16ቱ ክለቦች ተወካዮች በሚካፈሉበት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ላይ አስቀድሞ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላለማድረግና ምርጫው በቦርድ አመራርነት ብቻ ላይ ሊያተኩር ነው ተብሎ የተነገረ ቢሆንም ምርጫው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ማካተቱን ሀትሪክ አረጋግጣለች።
ሊግ ኩባንያው በ2012 በነበረውና በአቶ ኢሳያስ ጅራና በኮሎኔል አወል አብዱራሂም ፕሬዝዳንትና ም/ል ፕሬዝዳንትነት አመራር ዘመን ክለቦች ራሳቸው ውድድራቸውን እንዲመሩ ፍቃድ ከተሰጣቸው ቀን ጀምሮ ማህበሩን ከመመስረት አንስቶ ጠንካራ ስራዎችን እስከመስራት የደረሱበትን ተግባር መከወናቸው ታውቋል።
በነገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከምርጫው ውጪ ጠቅላላ ካፒታል ማሳደግ፣ የአክሲዮኑን ህግ ማሻሻያ ላይ መወያየት፣ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሰነዱን ማጸደቅ እንደሚከናወን ሀትሪክ ያገኘችው መረጃ ያስረዳል።
አስተያየት ይስጡ