በትላንትናዉ እለት በዝናብ ምክንያት ከእረፍት መልስ ሳይደረግ የተቋረጠዉ የሲዳማ ቡና እና የወላይታ ዲቻ ጨዋታ በዛሬዉ እለት ተካሂዶ ያለ ጎል ተጠናቋል።
ገና ጨዋታው መካሄድ ከመጀመሩ ዝናብ በመዝነቡ የተነሳ ሁለቱም ቡድኖች በዝናብ ታጅበዉ ጨዋታቸዉን ለማካሄድ የተገደዱ ሲሆን እንዲሁም ጨዋታው በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ከወትሮዉ በበለጠ መልኩ በበርካታ ደጋፊዎች የተሞላ ነበር።
በጨዋታዉ ላይ የሁለቱም ክለቦች እንቅሰቃሴ የተሻለ የነበረ ሲሆን ገና ከጅምሩ ወላይታ ዲቻዎች ለጎል የቀረበ ኳስ በአበባየዉ አጂሶ በኩል በመሞከር ቀዳሚዎቹ ነበሩ።
- ማሰታውቂያ -
በሜዳዉ ላይ እየጣለ በነበረዉ ዝናብ ምክንያት ሁለቱም ክለቦች እንደ ልባቸዉ ኳስን አንሸራሽረዉ ለመጫወት ሲቸገሩ ነበር።
በሲዳማ ቡናዎች በኩል ፊሊፕ አጃህ ከርቀት ሞክሮ የወላይታ ዲቻዎቹ ግብ ጠባቂ የመለሰበት ኳስ በሲዳማዎቹ በኩል የመጀመሪያቸዉ ሙከራ ሆኖ ተመዝግቧል።
ከእዛ በኋላ ሁለቱም ክለቦች ተጭነዉ መጫወትን የሞከሩ ሲሆን ተደጋጋሚ ለጎል የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም በዝናቡ ምክንያት ኳሷን እንደ ልባቸዉ መጫወት ሳይችሉ የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ጎል 0-0 በሆነ ዉጤት ተጠናቆ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
በእረፍት ሰአት ላይ የእለቱ ዳኞች ሜዳዉ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ጨዋታዉን ማስቀጠል እንደሚችል እና እንደማይችል ለማረጋገጥ በሜዳዉ ዉስጥ ኳስ እያነጠሩ ምልከታ ካደረጉ በኋላ ሜዳዉ ጨዋታዉን ለማስቀጠል ብቁ አለመሆኑን አረጋግጠዉ ቀሪዉ የ45 ደቂቃ ጨዋታ በይደር ለዛሬ 7:00 ሰአት ተላልፏል።
ከእረፍት መልስ በትላንትናው እለት ሳይካሄድ የቀረዉ ቀሪው 45 ደቂቃ ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ መካሄድ ጀምሯል።
ከትላንትናዉ ቀጥሎ የተደረገዉ የዛሬዉ ጨዋታ በእንቅስቃሴ ረገድ ከትላንቱ ይልቅ ደካማ እንቅስቃሴ በሁለቱም ክለቦች በኩል ሲስተዋል የነበረ ሲሆን በአንፃሩ የመጀመሪያዎቹን ደቂቃዎች ለጎል የቀረበ ሙከራ በማድረግ ረገድ ወላይታ ዲቻዎች በአንፃሩ የተሻሉ ነበር።
እንዲሁም የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች ሲዳማ ቡናዎች የተሻሉ በመሆን ተጭነዉ ወደፊት አዘንብለዉ መጫወት የጀመሩ ሲሆን ለጎል የቀረበ ኳስ ደጋግመዉ መሞከር ቢችሉም ጎል ሳይቆጠር ቀርቶ የእለቱ ጨዋታ እንቅስቃሴዉ ከትላንትናዉ ያነሰ ሆኖ ጨዋታው ያለ ጎል 0-0 በሆነ በእኩል ዉጤት ተጠናቋል።