መነሻ ገጽ ዜናዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት ለእግርኳስ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋገጡ “ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር እናመሰግናለን” አቶ ደረጄ አረጋ /የአ/አ እግርኳስ ፌዴ ፕሬዝዳንት/
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት ለእግርኳስ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋገጡ “ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር እናመሰግናለን” አቶ ደረጄ አረጋ /የአ/አ እግርኳስ ፌዴ ፕሬዝዳንት/

አጋራ
አጋራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
መንግስት ለእግርኳስ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋገጡ

“ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር
እናመሰግናለን”
አቶ ደረጄ አረጋ
/የአ/አ እግርኳስ ፌዴ ፕሬዝዳንት/

የመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ እግርኳሳዊ ዕድገትን ለማጠናከርና ከተማዋ ላይ ያለውን የሜዳ ዕጥረት ለማስወገድ የሚቻለውን እንደሚያደርጉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ፕሪሞ ሜዳ ላይ ባርኔሮና ልደታ ክፍለ ከተማ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በልደታ ክፍለ ከተማ 2ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀውን ጨዋታ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቦታው ተገኝተው መከታተላቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክለቦቹም ጋር የተወያዩ ሲሆን ለቀረበላቸው ጥያቄም በሰጡት ምላሽ መንግስት እግርኳሱን ለማበረታታት ቆርጦ መነሳቱን ገልጸው የከተማዋን እግርኳሳዊ ዕድገትን ለማጠናከርና ያለውን የሜዳ ዕጥረት ለማስወገድ ድጋፉን እንደሚያደርግ አረጋግጠውላቸዋል።

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ አረጋ በበኩላቸው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘት መደሰታቸውን ገልጸው ” ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር እናመሰግናለን። እኛም እግርኳሱን ለመምራት የተሰጠንን ሃላፊነት በመወጣት ዕውቀታችን ለእግርኳሳችን በሚለው መርሃችን መሰረት የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል።

የባርኔሮ ዋና አሰልጣኝ ጸጋ ማሞ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፕሪሞ ሜዳ ተገኝተው በሰጡት ማበረታታትና እግርኳሱ አንዱ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመግለጻቸው አመስግኖ ፌዴሬሽኑ የከተማውን እግርኳስ ከማነቃቃት አንጻር ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እየሰራ ያለውን ስኬታማ ስራ አወድሷል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት 15 ሜዳን” በአካል ተገኝተው ማስመረቃቸው ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...