የዋሊያዎቹና የሱዳን የዛሬ ጨዋታ
በሶማሌ ዳኞች ይመራል
“ፊፋ የወዳጅነት ጨዋታን የሌላ ሀገራት ዳኞች ካልመሩት አይመዘገብም ብሎናል”
የኢት.እግርኳስ ፌዴሬሽን
ኢንተርናሽናል የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደዋናው ውድድር የሌላ ሀገር አርቢትሮች ካልመሩት ወጤቱን እንደማይመዝግብ ፊፋ አስታወቀ።
ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ላይ እንደገለጸው “ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ሁለት ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርጉ የአስተናጋጁ ሀገር ዳኞች ይመሩት የነበረ ሲሆን ፊፋ ለአባል ሀገራት በሰጠው አዲሱ መመሪያ መሠረት በሀገራት የወሩ ደረጃ ላይ መመዝገብ የሚችሉት ጨዋታዎች ከተጋጣሚዎቹ ሀገራት ውጪ የሆኑ አርቢትሮች ከመሩት ብቻ መሆኑን ገልጾልናል” ሲል አስረድቷል።
- ማሰታውቂያ -
ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት በአበበ ቢቂላ የሚደረገው የኢትዮጵያና የሱዳን ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታን የሱማሌ ዳኞች የሚመሩት ሲሆን ዳኞቹ ሌላ ሀገር የተካሄደን ጨዋታ መርተው ሲመለሱ አዲሰ አበባ ላይ ትራንዚት የሚያደርጉ በመሆናቸው ፌዴሬሽኑ ከከፍተኛ ወጪ ተርፏል።