ቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች እያሉት አስቀድሞ ወደ ታችኛዉ ሊግ መዉረዱን ያረጋገጠዉ ለገጣፎ ለገዳዲ በአማኑኤል አረቦ ብቸኛ ጎል አዳማ ከተማን 1-0 በሆነ ዉጤት አሸንፏል።
የ26ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ የሆነዉ ዛሬ ረፋድ በለገጣፎ ለገዳዲ እና በአዳማ ከተማ መሀከል ተካሂዷል።
ጨዋታዉ ከወትሮ በተለየ መልኩ በተቀዛቀዘ መልኩ የተጀመረ ሲሆን ለተመልካቹም ሳቢ የነበረ አይደለም። የመጀመሪያ አጋማሽ የመጀመሪያ አከባቢ በአዳማ ከተማ ለጎል የሚሆኖ ከተሞከረዉ ኳስ ዉጪ የጨዋታዉ ክፍለ ግዜ አሰልቺ የሚባል አይነት ነበር።
- ማሰታውቂያ -
የመጀመሪያዉ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ግዜን አዳማ ከተማዎች ከሜዳቸዉ በመነሳት ወደፊት እየተጫወቱ የለገጣፎ ሜዳ ላይ የበላይነት ለመቆጣጠር ሲጫወቱ የነበረ ሲሆን እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲዎች በበኩላቸዉ የፍለፊት መስመር አጥቂዎቻቸዉን ያማከለ አጨዋወት ለመጫወት ሙከራ እያደረጉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ ያለ ጎል 0-0 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።
ሁለተኛዉ አጋማሽ ላይም ከመጀመሪያዉ አጋማሽ የተሻለ ነገር በሜዳ ሲስተዋል ያልነበረ ሲሆን በአመዛኙ ለጎል የሆነ ኳስ በመሞኮረ ረገድ ለገጣፎ ለገዳዲ የተሻለ ነበር።
በ72ኛ ደቂቃ አዳማ ከተማዎች ቦና እና ቢኒያምን አስወጥተዉ ዮሴፍ እና አሜንን ወደ ሜዳ ያስገቡ ሲሆን ከመጀመሪያዉ በአመዛኙ የተሻለ አጨዋወት ማድረግ የቻሉ ሲሆን ለጎል የሚሆን ኳስ ተቀይሮ የገባዉ ዮሴፍ በለገጣፎ ለገዳዲዎች ላይ ሞክሩ በግብ ጠባቂዉ የከሸፈበት ለአዳማዎች የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር።
መደበኛዉ የጨዋታ ክፍለ ግዜ 0-0 በሆነ ዉጤት ይጠናቃል ተብሎ ሲጠበቅ በተሰጠዉ ተጨማሪ ደቂቃ ላይ በቀሩት ሽርፍራፊ ሰከንዶች ዉስጥ አማኑኤል አረቦ ለለገጣፎ ለገዳዲዎች ጎል አስቆጥሮ ጨዋታዉ በለገጣፎ ለገዳዲ 1-0 ዉጤት አሸናፊነት ተጠናቋል።