መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ኢትዮጵያ ቡና ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ኢትዮጵያ ቡና ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ን ያሰናበተው በተገቢው መንገድ ነው ሲል ወሰነ።

አሰልጣኙ ከውል ውጪ ተሰናብቻለሁ ዲሲፕሊን ኮሚቴ መብቴን ያስከብርልኝ በማለት ክስ ያቀረበ ሲሆን ዲሲፕሊን ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ከአሰልጣኙ ጋር በውስጥ የተፈራረመውን ውል ፌዴሬሽን ሄደው ከፈረሙት ውል ጋር በጋራ በማጸደቁ የስንብት ርምጃው ተገቢነት ሲል ብይን መስጠቱ ታውቋል።

ብዙ ክለቦች ከአሰልጣኞች ጋር ውል ሲገቡ ከዋናው ውል ውጪ ውጤት ከጠፋ ስለሚሰናበትበት በስምምነት ስለሚለያዩበት የሚስማሙበትን ውል ፌዴሬሽን ሄደው ስለማያጸድቁ በራሳቸው ተስማምተው የፈረሙት የውስጥ ውል ውድቅ ሆነው በተደጋጋሚ ሲቀጡ መታየታቸውን የታዘበው የመረጃ ምንጩ በሊጉ የሚገኙ ክለቦች ከኢትዮጵያ ቡና ሊማሩ እንደሚገባ መክሯል።

ከሁለቱ ወገኖች አንደኛው ወገን ውል ማቋረጥ ከፈለገ ከአንድ ወር በፊት አስቀድሞ ተናግሮ ስምምነቱን ማቋረጥ ይቻላል በሚለውና በጸደቀው ውል መሠረት ለአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ህዳር ላይ ውሉን አቋርጦ ከታህሳስ 1/2015 ጀምሮ እንዳሰናበተው ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...