16ቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ደጋፊዎች የሚሳተፉበት አመታዊ የደጋፊዎች የእግርኳስ ውድድር እንዲካሄድ የሚያስችል ስምምነት መፈጸሙ ተነገረ።
ብራና ማስታወቂያ ሃ/የተወሰነ የግል ማህበርና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ደጋፊዎች ማህበራት ጥምረት መሃል ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በተደረገው ስምምነት መሰረት የደጋፊዎች አመታዊ የእግርኳስ ውድድር ከዘንድሮ አመት ጀምሮ በየአመቱ እንዲካሄድ የሚያስችል የጋራ ስምምነት መሆኑ ታውቋል።
ስምምነቱ በጥምረቱ አባል በሆኑ ደጋፊዎች መሃል መልካም ግንኙነትን መፍጠርና የእግርኳስን የሰላም አምባሳደርነት ማሳየት መሆኑ መሆኑን በብራና በኩል ስምምነቱን የፈረሙት አቶ በፍቃዱ ዓባይና አቶ ሄኖክ ተሾመ እንዲሁም የጥምረቱ ፕሬዝዳንት አቶ ደነቀው በሪሁን መግለጻቸው ታውቋል።
ሁለቱም ወገኖች በቀጣይ ስለውድድሩና ተያያዥ ጉዳዮች ጋዜጣ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።