ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 27ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 23 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 21 በጨዋታ ሁለት በራስ ላይ ነው። በሳምንቱ 26 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ግንቦት 28 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ውጤት በማፅደቅ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።
- ማሰታውቂያ -
በተጫዋችና ቡድን አመራሮች ደረጃ በተላለፉ ውሳኔዎች 3 ተጫዋቾችና ላይ ቅጣት ተላልፏል። አድናን ረሻድ(አዳማ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ፥ አሸናፊ ፊዳ(አርባምንጭ ከተማ) እና ካሌብ በየነ(ሀዲያ ሆሳዕና) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከታቸው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
በክለቦች ደረጃ በታዩ ሪፖርቶችም በሶስት ክለቦች የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል። አዳማ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ፥ ሲዳማ ቡና በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦየቀረበበት የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ፥ መቻል ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ የክለቡ ደጋፊ ተመልካችን በቦክስ ስለመማታቱና ሁከት ስለማስነሳቱ ሪፖርት የቀረበበት
በመሆኑ የክለቡ ደጋፊ በዕለቱ ለፈፀመው ጥፋት ክለቡ(መቻል) በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 25000/ሃያ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።