ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ዱሬሳ ሹቢሳ በልጅነት ለተጫወተበት አካዳሚ የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።
በቅርቡ ሰበታ ከተማን በመልቀቅ ባህር ዳር ከተማን የተቀላቀለው ፈጣኑ አጥቂ ወደ ትውልድ ከተማው ሻሸመኔ ሲመለስ ከልጅነት ክለቡ ሲቪዮ አካዳሚ የቡድን አባላት ጋር ልምምድ ሰርቷል ።
- ማሰታውቂያ -
ከልምምዱም በተጨማሪ ለሰላሳውም የቡድኑ አባላት የማሊያ ትጥቅ እንደሚያሟላቸውም ቃል ገብቷል።
ሲልቪዮ አካዳሚ እንደ ጫላ ተሺታ ዳዊት ተፈራ(ኦዚል) ፋሲል ባቱ እንዲሁም አዲስአለም ደሳለኝን ያፈራ አካዳሚ ነው ።እነዚህ ለሀገራችን እግር ኳስ ያበረከተው ደግሞ የሲልቪዮ አካዳሚ ዋና አሰልጣኝ መስፍን አበበ ይባላል።