በ2016 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀዳሚ ጨዋታ በከተማው ላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመክፈቻ ጨዋታውን ያደረገው አዳማ ከተማ 0 – 0 ተለያይቷል ።
ከጨዋታዉ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው የአዳማ ከተማው አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በተጫዋቾቹ አቋም ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል ።
በጨዋታው ላይ የነበረውን የነባር እና አዳዲስ ተጫዋቾች እንቅስቃሴ መልካም እንደነበር ተናግሯል ።
“እንደሚታየው ከኋላ ክፍሉ ሙሉ ነው የፈረሰው የገቡትም ልጆች በተፈጥሯቸው በመሀል ተከላካይ ቦታ ላይ ተጫውተው አያውቁምና ከኋላ እንደአዲስ ነው የምሰራው ። ጥሩ ናቸው ከጠበኩት በላይ ነው ያገኘዋቸው ።”
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኙ ቀጣዩን ጨዋታ እስከሚያደርጉበት ቀን ድረስ ባለው ጊዜ አስካከክለው የሚመጡትን ነገር በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም ተከታዩን መልስ ሰጥቷል ።
“አንዳንድ ችግሮች ይቀረፋሉ በእርግጠኝነት ። ሁለተኛ የመዘጋጃ ጊዜ እናገኛለን ። አንዳንድ ውጣውረዶች ነበሩ ። እነዛን ነገሮች አስተካክለን ተከላካዩም ፣ መሀሉም ፣ ማጥቃት ላይም የምንጫወተው ቢያንስ ከዚህ ከፍ ያለ ቡድን ይዘን እንመጣለን ። ለአሁኑ ግን ከበቂ በላይ ነው በጣም ነው ደስ ያለኝ ። ”
የሊጉ የመጀመሪያ 8 ሳምታት ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ ይደረጋሉ ። ይህም ከየትኛውም ቡድን በላይ ለአዳማ ከተማ የሜዳ ላይ ተጠቃሚነቱን እንደሚያጎላው ይጠበቃል ።
ከዚህ ቀደም ግን በሊጉ እንደሚታየው በከተማቸው የሚጫወቱ ክለቦች ነጥብ ለመሰብሰብ ሲቸገሩ ይስተዋላል ። አሰልጣኝ ይታገሱ ይህን እንቀይራልን ሲል ተናግሯል ።
“ተጫዋቾቹ በደጋፊ ፊት መጫወት ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ የሚያሳዩበት ነው ። በሁለተኝነት ሜዳው ለሁለታችንም እኩል ነው ። እንደልምድ ባለፉት አመታት የአዘጋጅ ከተማ ክለቦች በሜዳቸው ነጥብ ይጥላሉ ። ያንን ነገር እኛ እንቀርፋለን ብዬ አስባለሁ ። ”
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ ከጨዋታው ቀደም ብሎ በሰጠው አስተያየትም ቡድኑ ላለፉት ሶስት ቀናት ልምምድ አለመስራቱን ተናግሯል ።