በ2010 መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ ላለፋት ሁለት ዓመታት የምዓም አምበሶች ግብ ክልልን የጠበቀው ፊሊፕ ኦቮኖ ቀጣይ ውድድር ዓመት ከመቐለ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት መድረሱ የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ አድራሻ አስታውቋል።
የኢኳቶሪያል ብሄራዊ ቡድን አንደኛ ተመራጭ የሆነው ኦቮኖ መቐለ 70 አንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን አንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ተጨዋቾች በቀዳሚነት ሚጠቀስ ነው።
የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቐለ እያካሄዱ ሚገኙት የገብረመድህን ሃይለ ስብስብ በሚቀጥሉት ቀናት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ስሙ እየተያያዘ ያለውን የእጥቂያቸው አማኑኤል ገብረሚካኤል ውልን ለማራዘም ከተጨዋቹ ጋር ድርድር ሊያደርጉ አንደሚችሉ ይገመታል