ጥሎ ማለፍ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ከተጀመረ 79 አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በ2009 በጥሎ ማለፉ የዋንጫ ጨዋታ የተገናኙት መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ ናቸው የሁለቱን የዋንጫ ተፋላሚዎች የጥሎ ማለፍ ታሪካቸው ምን ያህል ግዜ ለፍፃሜው ደርሰዋል እሚለውን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ታቀርባለች
መከላከያ እግር ኳስ ቡድን በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በበአምስት ተከታታይ አመታት ለፍፃሜው ሲደርስ ለአምስተኛ ግዜ ነው፡፡
ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ በጥሎ ማለፍ ለፍፃሜ ሲደረስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ ወላይታ ድቻ በጥሎ ማለፉ የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው በ2007 ሲሆን በሀዋሳ ከተማ ተሸንፎ ከውድድሩ ወጪ ሊሆን ችልዋል፡፡
በመከላከያ በኩል በበ2005 ዓ.ም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በመደበኛው ሰዓት 0-0 ሲጠናቀቅ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት መከላከያ አሸንፏል፡፡ በበ2007 ዓ.ም ከሀዋሳ ከተማ ጋር፡ተገናኝቶ በ2:0 ውጤት ማሸነፈ ችሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
መከላከያ ዘንድሮ በኮንፌዴሬሽኑ እሚሳተፍበትን ውጤት ያገኘው አምና ሰኔ 30 በ2008 ዓ.ም በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም ከኘሪሜየር ሊጉ አሸናፊ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በመደበኛው የጨዋታ ሰዓት 1-1 ተጠናቆ በፍፁም ቅጣት ምት በፈረሰኞቹ ቢሸነፍም ዘንድሮ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያ ወክሎ በካሜሮኑ ያንግ ስፖርት አካዳሚ በደርሶ መልስ ውጤት 2-1 ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ወጪ መሆኑ እሚታወስ ነው፡፡