ከግማሽ በላይ ቋሚ ተሰላፊዎቹን ያጣው ድሬዳዋ ከተማ የወቅቱ ስድስተኛ ፈራሚያቸውን ያሬድ ሃሰንን አድርገዋል።
ከመቐለ 70 አንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ያሬድ ሃሰን ባሳለፍነው ውድድር ዓመት በግራ ተከላካይ መስመር ላይ ከአንተነህ ገብረክርስቶስ እና ሄኖክ ኢሳያስ ጋር እየተፈራረቁ መጫወት ችሏል።
ቀደም ብለው ፍሬዘር ካሳን ያስፈረሙት ድሬዎች ያሬድ ሃሰንን ማስመጣታቸው በግራ መስመር ተከላካይ ያላቸውን አማራጭ ሊያሰፋላቸው እንደሚችል ይገመታል።ዋለልኝ ገብረ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ዘሪሁን አንሼቦ፣አማኑኤል ተሾመ፣ዘካርያስ ቱጂ በያዝነው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ድሬዳዋን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች ናቸው።
- ማሰታውቂያ -
በሳምሶን አባይ ሚመሩት ድሬዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መስከረም 10 መቐለ ላይ ይጀምራሉ።