የምንተስኖት አሎ የመጀመሪያ ቀን የቱርክ ሙከራ
የስሑል ሽረ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ምንተስኖት አሎ ዛሬ የመጀመሪያ ሙከራውን ጀምሯል።
ከትላንት በስትያ ባገኘው የፕሮፌሽናል ተጫዋችነት የሙከራ ግዜ ለማድረግ ቱርክ ኢስታምቡል የደረሰው ምንተስኖት አሎ። በቱርክ ዋናው ሊግ ለሚሳተፍ አንታሊያስፖር አንካራ እና በሁለተኛ ሊግ ለሚሳተፈው ደሚርስፖር ለአንድ ሳምንት ያክል ሙከራ የሚደርገው ወጣቱ ግብ ጠባቂ ዛሬ የመጀመሪያ ሙከራውን ጀምሯል። ሙከራውም ጥሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ከርቀት የሚላኩ ኳሶችን መቅለብ እና የምልስ ምቶችን መለጋት በመጀመሪያ ቀን ውሎው ካከናወናቸው ሙከራዎች ናቸው ። ለተስፈኛው ግብ ጠባቂ ሀትሪክ ስፖርት መልካም ምኞቷን ትገልፃለች።