የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ
በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ቀሪ ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላሉ።
አ/አ ላይ በሚደረገው በቅዳሜ ብቸኛ የሊጉ ተስተካካይ ጨዋታ 10፡00 ሲል ኢትዮጵያ ቡናን ከ ሀዋሳ ከተማ የሚያገናኝ ይሆናል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሁለት የተለያየ የጨዋታ ዝግጁነት ላይ በሚገኙ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ሲሆን ኢት. ቡና ከሁለት ተከታታይ ድሎች በኋላ ወደ መቐለ ተጉዞ ከመቐለ ከተማ ጋር አቻ ተለያይቶ የተመለሰ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ በአንፃሩ ያለፈውን ሳምንት ጨዋታውን ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። ኢትዮጵያ ቡና በጥሩ መነቃቃት ላይ ሲገኝ ሀዋሳ ከተማ በወጥ አቋም ሊጉ ላይ መጓዝ ሲያቅተው ተስተውሏል። በዘንድሮው የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ እንደ ሀዋሳ ከተማ ብዙ የኳስ ቁጥጥሮችን አሳክቶ ግን ወደ ግብነት በመቀየሩ ረገድ ደካማ የሆነ ቡድን አልታየም።
- ማሰታውቂያ -
በ15ኛው ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወደ ወደ መቐለ ተጉዞ ከመቐለ ከተማ ጋር አቻ የተለያዩ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ በአንፃሩ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ማድረግ የነበረበትን የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ በነበረበት የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ምክንያት ወደ የካቲት 22/ 2010ዓ.ም በመዛወሩ ምክንያት ሳያከናውን ቀርቷል።
ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮው የሊጉ ጉዞ በሜዳው ባደረጋቸው ጨዋታዎች በደጋፊው እየታጀበ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን በተቃራኒው ሀዋሳ ከተማ ደግሞ ከሜዳው ውጪ አስከፊ ጉዞ እያደረገ ይገኛል።
በአጠቃላይ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከ15 ጨዋታዎች 14 ጨዋታዎችን አድርጎ አራቱን በማሸነፍ አራቱን አቻ ወጥቶ በአምስቱ ተሸንፎ በ19 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። ሀዋሳ ከተማ በአንፃሩ 13ጨዋታዎችን አድርጎ 3ጨዋታዎችን አሸንፎ 5ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ 5ጨዋታዎችን ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 39ነጥቦች 14ቱን አሳክቶ ከተጋጣሚው በ5ነጥቦች ርቆ 11ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የነበሩት አክሊሉ አየነው፣ አለማየሁ ሙለታ፣ ሮቤል እና አስቻለው ግርማ አሁንም ለቡድናቸው ግልጋሎት የማይሰጡ ሲሆን አማኑኤል ዮሀንስ ደግሞ በሀዘን ምክንያት የማይኖር ይሆናል። ከሀዋሳ ከተማ በኩል ግብ ጠባቂው ተ/ማርያም ሻንቆን ጨምሮ ሳዲቅ ሴቾና ያቡን ዊሊያም በረጅም ጉዳት የሚያጣ ሲሆን ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ የላውረንስ ላርቴ እና ዳንኤል ደርቤ የመግባት ጉዳይ 50/50 ነው፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ልክ 10:00 ሲል በ አ/አ ስታዲየም ላይ የሚጀምር ይሆናል።
ጨዋታውን የሚመሩ ዳኛ፡ ሰለሞን ገ/ሚካኤል