በህዳር ወር ለሚጀምረው ለ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት የቅዱስ ጊዮርጊስ እንስቶች አንድ አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስባቸዉ ሲቀላቅሉ የአራት ተጫዋቾችን ዉል ደግሞ አድሰዋል።
በዚህም መሰረት ፈረሰኞቹ ሰርካዓለም ሻፊን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ሲያስፈርሙ እንዲሁም የቤተልሄም ጌታቸውን ፣ የሃናን ረዲን ፣ የመሰረት ገዛኸኝን እና የቃልኪዳን ወንድሙን ዉል አድሰዋል።