By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | ስድስት ግቦች በተስተናገዱበት ጨዋታ ሀይቆቹና ዓፄዎቹ ነጥብ ተጋርተዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግፋሲል ከነማ

የጨዋታ ዘገባ | ስድስት ግቦች በተስተናገዱበት ጨዋታ ሀይቆቹና ዓፄዎቹ ነጥብ ተጋርተዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 2 years ago
Share
SHARE

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ሲደረጉ ስድስት ግቦች በተስተናገዱበት ጨዋታ ፋሲል ከነማነሠ ሀዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል ።

በጨዋታው በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሚመራው ፋሲል ከነማ በኩል ሚኬል ሳማኪ ፣ መናፍ ዐወል ፣ ምኞት ደበበ ፣ ዮናታን ፍስሀ ፣ ዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ሱራፌል ዳኛቸው ፣ ሽመክት ጉግሳ ፣ ይሁን እንደሻው ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል እና ጌታነህ ከበደ በምርጥ 11 ተካተዋል ።

እንዲሁም በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በሚመራው ሀዋሳ ከተማ በኩል ፅዮን መርዕድ ፣ መድኃኔ ብርሀኔ ፣ ሰለሞን ወዴሳ ፣ ሚሊዮን ሰለሞን ፣ እንየው ካሳሁን ፣ ታፈሰ ሰለሞን ፣ አብዱልባሲጥ ከማል ፣ አማኑኤል ጎበና ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ እዮብ አለማየሁ ፣ አሊ ሱሌማን በመጀመሪያው አሰላለፍ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው ።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ፋሲል ከነማ ተሽሎ በታዩበት ጨዋታ ግብ በማስቆጠሩ ቀዳሚ መሆን ችለዋል ።

- ማሰታውቂያ -

በጨዋታው 9ኛ ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛ ከርቀት ያገኘውን የቅጣት ምት ለቡድን አጋሮቹ ያሻማል ተብሎ ሲጠበቅ በቀጥታ ወደ ግብ በመምታት ከመረብ አሳርፎታል ።

በማጥቃት እንቅስቃሴ የተሻሉ የነበሩት አፄዎቹ ከመጀመሪያው ግብ መቆጠር በኋላ ጥሩ ጥሩ የግብ ዕድሎች ለማግኘት ችለዋል ።

በ13ኛው ደቂቃ ላይ ሽመክት ጉግሳ ከሚሊዮን ሰለሞን የነጠቀውን ኳስ ለጌታነህ ከበደ ማቀበል ቢችልም አጥቂው ጌታነህ ከበደ ያገኘውን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

በሀዋሳ ከተማ በኩልም በተወሰኑ አጋጣሚዎች የፋሲል ከተማን የኋላ ክፍል ሰብረው በመግባት የግብ ዕድሎች ለመፍጠር ቢጥሩም በቀላሉ ሊያደርጉት አልቻሉም ።

በጨዋታው 20ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከበደ ለሱራፌል ዳኛቸው አቀብሎ ወደ ሳጥን ሲገባ ኳሱን ከሱራፌል የደረሰው ሽመክት ወደ መሀል ቀንሶት ጌታነህ ከበደ ኳስና መረብን አገናኝቷል ።

ሀይቆቹ በ36ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን የመጀመሪያ የግብ ዕድል መፍጠር የቻሉ ሲሆን ታፈሰ ሰለሞን ወደ ሳጥን ያሻገረውን ኳስ ሙጂብ ቃሲም በግንባር ገጭቶ ወደ ግብ ልኮት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል ።

የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ በፋሲል ከነማ የ2 – 0 መሪነት ሲጠናቅቅ በሁለተኛው አጋማሽ ግን የተለየ መልክን በመያዝ ነበር ።

ሀዋሳ ከተማዎች በሁለተኛው አጋማሽ ግብ ለማስቆጠር የፈጀባቸው 24 ሰከንዶች ብቻ ነበር ።

ከግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ የተነሳውን ኳስ የቀድሞው የፋሲል ከነማ ተጫዋች ታፈሰ ሰለሞን ከመረብ ላይ አሳርፎታል ።

ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ጌታነህ ከበደ ጥሩ የግብ ዕድል አግኝቶ ወደ ግብ የመታው ኳስ በፅዮን መርዕድ ተይዞበታል ።

ጨዋታው 55ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ አሊ ሱሌማን ከመጀመሪያውን ግብ አስቆጣሪው ታፈሰ ሰለሞን የደረሰውን ኳስ በግሩም ሁኔታ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ ከመረብ አሳርፎታል ።

ጫና ማሳደራቸው የቀጠሉት ሀዋሳ ከተማዎች በ80ኛው ደቂቃ ላይ ከ2 – 0 መመራት ወደ 3 – 2 መሪነት የተሸጋገሩበትን ጎል አስቆጥረዋል ።

የሁለተኛው ግብ አስቆጣሪ አሊ ሱሌማን ከቅጣት ምት ያሻገረውን ኳስ ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል በሳማኪ ሚኬል መረብ ላይ አስቆጥሮታል።

ሶስተኛውን ግብ ካስተናገዱ በኋላ የሀዋሳ ከተማን የኋላ መስመር ደጋግመው የፈተሹት ፋሲል ከነማዎች አቻ የሆኑበትን ግብ በ85ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል ።

የመጀመሪያውን ግብ በቅጣት ምት ያስቆጠረው ሱራፌል ዳኛቸው በድጋሚ ከቅጣት ምት ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ደግሞ ሶስተኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል ።

የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመሩት 4 ደቂቃዎች ላይ በረከት ሳሙኤል በአለምብርሀን ይግዛው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርድ ሲመለከት ከዕለቱ የመሀል ዳኛ ባህሩ ተካ ጋር በነበረው ንግግር በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ።

በመጨረሻም አዝናኛ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ከስድስት ግቦች ጋር ያስተናገደው ጨዋታው በ3 – 3 ውጤት ተጠናቋል ።

በሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው አርብ ጥቅምት 2 በ12:00 ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድኅን እንዲሁም እሁድ ጥቅምት 4 በ12:00 ሀዋሳ ከተማ ከሻሸመኔ ከተማ ይጫወታሉ ።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article World Cotton Day: FIFA to turn “world’s spotlight” on African cotton producers
Next Article የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ ዓመቱን በድል ጀምረዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሻሸመኔ ከተማዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት እለት ታዉቋል።

Biruk Hanchacha By Biruk Hanchacha 3 years ago
አዳማ ከተማ የአዲስ አበባ ቆይታውን ያለሽንፈት ሲያጠናቅቅ  ሸገር ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርተዋል !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከቡ ከወራቶች ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመልሷል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢብራሂም ፎፋናን የግሉ አደርጓል
“በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል” ዱላ ሙላቱ /ሀዲያ ሆሳዕና/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?