መነሻ ገጽ ለገጣፎ ለገዳዲ አፄዎቹ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል
ለገጣፎ ለገዳዲዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

አፄዎቹ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል

አጋራ
አጋራ

 

በአሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ የሚመራዉ ፋሲል ከነማ በናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ሁለት እና ፍቃዱ ዓለሙ አንድ ጎሎች ታግዞ አዲስ አዳጊዉን ለገጣፎ ለገዳዲን ሶስት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለወትሮዉ ለዋንጫ ፉክክሩ ቅድመ ግምት ከሚሰጣቸዉ ክለቦች መካከል ግንባር ቀደም የነበረዉ ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ደካማ የሚባል አጀማመርን በማድረግ ላይ ሲገኝ በዚህም በተለይ በአምስተኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን ከረታበት የጨዋታ ሳንትምት በኋላ ወደ ዉጤታማነት ለመመለስ እየተቸገረ ይገኝ የነበረዉ እና በዚህኛው የጨዋታ ሳምንት በንፅፅር ደካማ ከሚባለዉ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ያደረገውን ጨዋታም በድል መወጣቱን ተከትሎ በቀጣይ ለሚኖሩት የሊጉ መርሐግብር የቀኑ ጨዋታ በስነልቦናዉ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ ይጠበቃል።

በተቃራኒዉ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ በመሳተፍ ላይ የሚገኘዉ ለገጣፎ ለገዳዲ በሊጉ ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች አንድም ድል ማስመዝገብ ሳይችል ሲቀር በተቃራኒው አስራ አምስት ግቦች ተቆጥረዉበት በ ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጦ የእስረኛውን የጨዋታ ሳምንትም የሚቀበል ይሆናል።

ዉጤቱን ተከትሎም በዛሬዉ ጨዋታ ወደ አሸናፊነት የተመለሰዉ ፋሲል ከነማ በሰባት የሊጉ ጨዋታዎች አስራ አንድ ነጥቦችን ሰብስቦ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዲስ አዳጊዉ ለገጣፎ ለገዳዲ አራት ነጥቦች የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ተቀምጧል። በቀጣይ የአስረኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብርም በዛሬዉ ጨዋታ ድል የቀናዉ ፋሲል ከነማ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከሚመራዉ ሲዳማ ቡና ጋር ሲገናኙ ፤ በተመሳሳይ በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘዉ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተመስገን ዳናዉ ኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚጫወቱም ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...