አጋራ

በአሰልጣኝ ተመስገና ዳና የሚመራዉ ኢትዮጵያ ቡና ከሁለት ተከታታይ ድል አልባ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሱበትን ወጤት ኢትዮ ኤሌክትሪክን አራት ለሁለት በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ማስመዝገብ ችለዋል።

በጨዋታዉም በክረምቱ የተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት ክለቡን የተቀላቀለዉ እና እስከ ምሽቱ ጨዋታ ድረስ አንድም የሊግ ግብ ማስቆጠር ያልቻለዉ መሀመድ ኑር ናስር ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ፣ ኤርትራዊዉ አማካይ ሮቤል ተክለሚካኤል እና የፊት መስመር አጥቂዉ ብሩክ በየነ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች እስከአሁን ድረስ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ላልቻሉት እና በትላንትናው ዕለት በይፋ አሰልጣኛቸዉን ላሰናበቱት ኢትዮ ኤሌትሪኮች የፊት መስመር ተጫዋቹ ሔኖክ አየለ እና ልደቱ ለማ ሁለቱን የማስተዛዘኛ ጎሎች ከመረብ ማሰረፍም ችለዋል።

በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ስድስት ጎሎች ተቆጥረዉበት የነበረዉ የመዲናዉ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ወጥ በሆነ ብቃት ጨዋታዎችን በድል የመወጣት ጥያቄ እየተነሳበትም ቢሆን በስምንት ጨዋታዎች አስራ ሶስት ነጥቦችን ሰብስቦ በጊዜያዊነት ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፤ በምሽቱ ጨዋታ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ በዘጠኝ ጨዋታዎች አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ አስራ አምስተኛ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ በአስረኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብርም የተመስገን ዳናዉ ኢትዮጵያ ቡና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ከሚገኘዉ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ሲገናኙ ፤ በተመሳሳይ በደረጃ ሰንጠረዡ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘዉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኙ መቻል ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...