የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በአዳማ ከተማ – አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከ12ኛ እስከ 15ኛ ሳምንት እንደሚካሄድ ይታወቃል። ውድድሩ ሐሙስ ጥር 16/2016 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን የሁለቱ ቀን(ሐሙስ እና አርብ) አራት ጨዋታዎች ከዚህ በፊት በተገለፀው የ180 ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት ድልድል መሰረት የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አይኖራቸውም። የቀጥታ ስርጭት ቅዳሜ ጥር 18/2016 ዓ.ም ባለ የ12ኛ ሳምንት አምስተኛ ጨዋታ የሚጀምር ሲሆን ከዚህ ጨዋታ በኋላ ያሉ የአመቱ የሊጉ ጨዋታዎች በአጠቃላይ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይኖራቸዋል።
በዚህም መሰረት
ኢትዮጵያ መድን ከ ሻሸመኔ ከተማ
መቻል ከ ፋሲል ከነማ
ባህር ዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
- ማሰታውቂያ -
የቀጥታ ስርጭት የማያገኙ ጨዋታዎች ናቸው!!