የጉባዔ ቦታውን ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ የቀየረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በአፍሪካ ኢኮኖሚ አዳራሽ ተካሂዷል ።
ጉባኤው በባህልና ስፖረሰት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በመቀጠልም አጀንዳዎች ቀርበው የማፅደቅ ሂደት ተከናውኗል ።
በመቀጠልም የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለጉባኤው አባላት አቅርበዋል ። ከሪፖርቱ በኋላ የፌዴሬሽኑ የፋይናንስ ኃላፊ አቶ ነብዩ ደምሴ የዓመቱን የፋይናንስ ሪፖርት ማቅረብ ችለዋል ።
በጉባዔው በተለይም በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን አቶ አሊሚራ መሀመድ በተወዳዳሪነት መያዝ እና የአዲሱ ክልል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጉባኤው አባል መሆን ተቀባይነትን ማግኘት ችለዋል ።
- ማሰታውቂያ -
የዕለቱ ጉባዔ በመጨረሻም በወቅቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ንግግር አድርገው ተጠናቋል ።
በነገው ዕለትም በጉጉት የሚጠበቀው ለቀጣይ አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት እና በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩ ግለሰቦችን የሚያሳውቀው ምርጫ የሚካሄድ ይሆናል ።