By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር ተመሰረተ
Share
Notification Show More
Latest News
ሁለት ተጫዋቾች የአራት ጨዋታዎች ዕገዳ ሲጣልባቸው ሶስት ክለቦች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህርዳር ከተማ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….
አትሌቲክስ ዜናዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ወላይታ ድቻ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ ድሬዳዋ ከተማ
የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
አትሌቲክስዜናዎች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር ተመሰረተ

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 4 months ago
Share
SHARE

“ለአትሌቶቻችን ከሆቴላቸው እስከ አየር መንገድ ደማቅ አሸኛኘት እናደርጋለን ።”

“ለመረዳት ሳይሆን ፌዴሬሽኑን ለመርዳት የተቋቋመ ማህበር ነው ።”

“በግል ውድድሮችም ክብረወሰን ለሚያሻሻሽሉ አትሌቶች የክብር አቀባበል እናደርጋለን ።”

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር መስራች እና ፕሬዚዳንት አቶ ምንያህል ጌታቸው

- ማሰታውቂያ -

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ታሪክ ስማቸውን በደማቁ ካፃፉ እና በማፃፍ ላይ ካሉ ሀገራት ግንባር ቀደሟ ናት ። ይህ የስፖርት ዘርፍ ለሀገሪቱ የገፅታ ግንባታ እየተወጣ ያለው ሚናም ዕጅግ የላቀ ነው ።

መላው ኢትዮጵያዊም በአለም ሻምፕዮናዎች እና ኦሎምፒኮች ላይ በጀግኖች አትሌቶች በርካታ የደስታ ጊዜያትን አጣጥሟል ። ለዚህ የሀገራችን መለያ ለሆነው አትሌቲክስ ብዙዎች ዋጋ ከፍለው አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩን ሰንድቅ ከፍ አድርገው አሰቅለዋል ።

እነዚህን ጀግኖች በሞራል መደገፍ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ማገዝ ዓላማውን ያደረገው የአትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር “የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር” በሚል መጠሪያ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመስርቷል ።

በኔክሰስ ሆቴል በተደረገው የማህበሩ ምስረታ መርሐግብር ላይም በኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፤ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ ፤ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢንያም ምሩፅን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል ።

የማህበሩን ምስረታ አስመልክቶም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር መስራች እና ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ምንያህል ጌታቸው ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገፅ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገዋል ።

አቶ ምንያህል የማህበሩን መመስረት አላማ እንዲህ ገልፀውታል ። “ውጤት ሲመጣ ማንም ውጣ ሳይባል ሄዶ ይቀበላል ። ውጤት ሲጠፋ ደግሞ በዛው ልክ ወቀሳ ብቻ ይኖራል ። የማህበሩ መመስረት ለምንድነው ያስፈለገው ካልን ውጤት ቢመጣም ውጤት ቢጠፋም ፤ በህብረት በአንድነት ሆነን ፤ አንድ ላይ ቆመን በተቀናጀ መልኩ አቀባበል ለማድረግ ፤ ለረጅም ጊዜ የተረሱ አትሌቶች ከያሉበት ፈልገን ለማውጣት እና ለማገዝ ነው ። ስለዚህ ተደራጅተን አትሌቲክሱ ላይ ችግር እንኳን ቢፈጠር ወደ አደባባይ ከመውጣቱ በፊት እኛ መሀል ላይ ገብተን ጀግኖች የሮጡለትን ሰንደቅ አንጥፈን የማግባባት እና የማስማማት ስራ ነው የምንሰራው ። ”

እንደ ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ምንያህል ጌታቸው ገለፃ ማህበሩን ለመመስረት ከኦሪገኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና መልስ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ደጋፊዎች ማህበር በአቀባበሉ ወቅት ላደረጉት አስተዋጽኦ የተሰጣቸው ዕውቅና መነሻው ነበር ብለዋል ።

በመቀጠልም ስፖርቱ አካባቢ ያሉ ሰዎችን ፣ ባለሀብቶች ፣ የሙዚቃ ባለሙያዎች ፣ አርቲስቶች ፣ ጋዜጠኞች ፣ ስፖርቱ አካባቢ ያሉ የህግ ባለሙያዎች እና ሌሎችን በማካተት ማህበሩ መመስረቱን ተናግረዋል ።

ማህበሩ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በሚደረገው የቡዳፔስቱ 19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ አዲስ ነገር ይዘን እንደሚመጣም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል ።

“በቅርቡ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚደረገው የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አትሌቶቻችንን ከሆቴላቸው እስከ አየር መንገድ በማልያ እና በሰንደቅ አላማ አሸብርቀን ለመሸኘት ተዘጋጅተናል ። በማህበር ስትሆን እንደዚህ አይነት ጠንካራ ስራዎችን መስራት ትችላለክ ። ”

ይሀ ማህበር የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ለማግኘት ብቻ እንደተቋቋሙ ማህበራት የተቋቋመ አይደለም ሲሉም አቶ ምንያህል ያክላሉ ።
” ይህ ማህበር የተቋቋመው እርዳታ ለማግኘት ሳይሆን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለማገዝ ነው የተቋቋመው ። አቅም ያላቸው ገንዘብ ያላቸው ዕውቀት ያላቸው ሰዎችንም ይዘን ነው ማህበሩን የመሰረትነው ። ”

በተያያዘም በግል ውድድሮች ላይ ክብረወሰኖችን በማሻሻል ለሚያሸንፉ አትሌቶችም ደማቅ አቀባበል በማድረግ እስከማረፊያቸው ለማድረስ ተዘጋጅተናል ብለዋል ።

ግንቦት 5 ሙሉ ዕውቅና አግኝቶ በትናንትናው ዕለት ወደ ስራ የገባው ማህበሩ 28 መስራች እና 47 አባላት በድምሩ 75 አባላትን ይዟል ።

ማህበሩ ገና ከምስረታው የተመሰረተበትን አላማ በሚገባ በሚያሳይ መልኩ ለተስፈኛ አትሌቶች እና ለአንጋፋ አትሌቶች ድጋፎችን አድርጓል ።

አቶ ምንያህል እንደገለፁት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢንያም ምሩፅን በማማከር ለ20 የነገ ተስፋ ለሆኑ አትሌቶች ደረጃውን የጠበቀ የሙሉ ትጥቅ ድጋፍ ተደርጓል ።

በተጨማሪም ለአስር አንጋፋ አትሌቶች የ5 ሺህ ብር ስጦታ ፣ ቱታ እና የጫማ ድጋፍ አድርገናል ሲሉም አክለዋል ።

በዕለቱ መርሐግብር ለአትሌቲክሱ የአንበሳውን ድርሻ ለተወጡ በህይወት ለሌሉት የቀስተዳመና ባለቤት አቶ አቤሴሎም ፣ ለአቶ ጌታ ዘሩ እና ለአቶ ቢልልኝ መቆያ ማህበሩ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽን አትሌት ደራርቱ ቱሉ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚዎች ስጦታ አበርክተዋል።

ማህበሩ የስራ አስፈፃሚ አባላትን የሰየመ ሲሆን ፕሬዚዳንት አቶ ምንያህል ጌታቸው ፤ ምክትል ፕሬዚዳንት የህግ ባለሙያ እና ጠበቃ አቶ ፍፁም ወልደጊዮርጊስ ፤
ዋና ፀሀፊ ተዋናይት እና ሞዴሊስት ወ/ሮ ሂሩት ማንያዘዋል እንዲሁም አቶ መሀመድ አሊ እና አቶ ክንፈ በሻ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ ተካተዋል  ።

You Might Also Like

ሁለት ተጫዋቾች የአራት ጨዋታዎች ዕገዳ ሲጣልባቸው ሶስት ክለቦች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….

የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ሲዳማ ቡና የተከላካዩን ኮንትራት አራዝሟል!
Next Article ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ለረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክን ያንብቧት፤ አታምልጦት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ለንባብ ትበቃለች።

hatricksport team By hatricksport team 4 years ago
ቅ.ጊዮርጊስ ከሚገኝበት የካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የቱኒዚያው ኤስፔራንስ አሸነፈ
የአሰልጣኝ ስዩም አባተ የመታሰቢያ ዋንጫ በኢትዮጵያ ቡናና ንፋስ ስልክ ቡድኖች አሸናፊነት ተጠናቀቀ
አብዱልከሪም መሀመድ (ተርሚኔተር ) ወደ አፄዎቹ
ከ17 ዓመት በታች | የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ሐዋሳ ከተማ  የአዳማ አቻውን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?