በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው እና በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ አንጋፋው ክለብ ቅ/ጊዮርጊስ እና ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ቫዝፒንቶ በዛሬው እለት መለያየታቸውን የቅ/ጊዮርጊስ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ አሳውቋል።። አሰልጣኙ በቅ/ጊዮርጊስ ለ1 አመት ብቻ የቆዩ ሲሆን በእርሳቸው የአሰልጣኝነት ዘመን ክለቡ ከ4 ተከታታይ አመታት ሻምፒዮንነት በኋላ በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ በኢትዮጵያ ዋንጫ(በጥሎ ማለፍ) ደግሞ በመከላከያ ተሸንፎ ሁለተኛ ወጥቷል። ይህንንም ተከትሎ ክለቡ ከ2006 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ውድድሮች ውጪ የሆነበትን ታሪክ ያስመዘገበው በእኚሁ አሰልጣኝ ነው። አሰልጣኙ በክለቡ በነበራቸው ቆይታ ቅ/ጊዮርጊስን ኳስ ተቆጣጥሮ የሚጫወት ቡድን ለማድረግ እና ደጋፊው የሚፈልገው አይነት አጨዋወት ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል። ሆኖም ክለቡ የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማሬውን በሚያደርግበት እለት ከአሰልጣኙ ጋር መለያየቱ የክለቡን ደጋፊዎች። እና ብዙውን የእግርኳስ ተመልካቾች ግርምት ውስጥ ከቷል። ክለቡም ከተለያዩ አሰልጣኞች ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።