የጨዋታ ቅድመ- እይታ | ወልዋሎ አ.ዮ ከ ወልቂጤ ከተማ

የኢትዮጽያ ፕሪምየር ሊግ 15ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ በሚደረጉ 5 ጨዋታዎች ሲቀጥል፤ወልዋሎ እና ወልቂጤ ከተማ የሚያገናኘውን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ:- ወልዋሎ ከ ወልቂጤ ከተማ
የጨዋታ ቀን :- እሁድ የካቲት 14/2012
የጨዋታ ቦታ :- ወልዋሎ ስታድየም
የጨዋታ ሰዓት :- 9:00
የጨዋታ ዳኛ ፦ ፌደራል ዳኛ ኢሳያስ ታደሰ

ቢጫ ለባሾቹ ከ1 ዓመት ስድስት ወር ቆይታ በኃላ ወደ አዲግራት ተመልሰው በሜዳቸው ወልዋሎ ስታድየም ወልቂጤ ከተማን ሚያስተናግዱ ይሆናል።የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ሚገኙት ወልዋሎዎች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ወልቂጤዎች በበኩላቸው ባሳለፍነው ሳምንት በሜዳቸው በሲዳማ ቡና የተነጠቁትን ነጥብ ለማካካስ ከፍተኛ ፋክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አራት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኃላ ወደ ልምምድ የተመለሱላቸው ወልዋሎዎች በነገው ጨዋታ ብዙ የተጨዋቾች ለውጥ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።በረዳት አሰልጣኞቻቸው እየተመሩ ሊከተሉት የሚችሉት የጨዋታ ስልት ለመገመት ከባድ ቢሆንም በሜዳቸው እንደመጫወታቸው ማጥቃት ላይ መሠረት ያደረገ ስልት ይዘው ሊገቡ ይችላሉ።በተለይ ብሩክ ሰሙ፣ኢታሙና ኬይሙኔ እና ጁንያንስ ናጋንጂቦ መሀከል ሚኖረው ቅንጅት የወልዋሎዎች የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ሚኖረው ይሆናል።

መጨረሻ ላይ ካደረጉዋቸው 5 ጨዋታዎች 10 ነጥቦችን መሰብሰብ የቻሉት በደግአረግ ይግዛው ሚመሩት ወልቂጤዎች በነገው ጨዋታ ጥንቃቄ የታከለበት አጨዋወትን መርጠው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።እንደነ ጫላ ተሺታ፣አህመድ ያሲን እና ሳዲቅ ሴቾ ፈጣን ተጨዋቾች ያልዋቸው ወልቂጤዎች መስመር ላይ ትኩረት ባደርገ መልሶ ማጥቃት እድሎችን ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወልዋሎዎች አይናለም ሀይሉ፣ካርሎስ ዳምጠው፣ፍቃዱ ደነቀን ከጉዳት መልስ ሲያገኙ ሰመረ ሀፍታይን አሁንም በጉዳት ሲያጡ፤ክትፎዎቹ በበኩላቸው የአማካያቸውን ፍፁም ተፈሪ ግልጋሎት ማያገኙ ይሆናል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer