የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥር 04 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አራቱ በመሸናነፍ ቀሪ አራቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 10 ጎሎች ተቆጥረዋል። 38 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል ።
በተጫዋቾች በተላለፉ ውሳኔዎች – ብሩክ ቃልቦሬ(ሀምበሪቾ) ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በ38 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
በክለቦች ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ – ሀምበሪቾ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋቾች የሆኑት ብሩክ ቃልቦሬ ፣ ፀጋሰው ዴማሙ ፣ ዳግም በቀለ ፣ ትግስቱ አበራ እና ፓሉማ ፓጁ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ፥ ወልቂጤ ከተማ በነበረው የ10ኛ ሳምንት ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኞችንና የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።