ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ በመጪው ሰኔ 4 የሚደረገውን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ እንዲመራ ተመርጧል ።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሞሮኮ እና ግብፅ ላይ የሚደረጉትን የ2023 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የደርሶ መልስ የፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞችን ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያዊን የመሀል ዳኛ ባምላክ ተሰማን በሞሮኮ የሚደረገውን ሁለተኛውን የመልስ ጨዋታ እንደሚመራ ይፋ አድርጓል ።
በሞሮኮ መሀመድ ስድስተኛ ስታድየም በሚደረገው ጨዋታ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ የግብፁን አል አህሊ ያስተናግዳል ።
በአህጉሪቱ ታላላቅ የተባሉ የክለቦችም ሆነ የሀገራት ጨዋታዎችን በብቃት በመዳኘት የሚታወቀው ባምላክ ተሰማ ከዚህ ቀደምም በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ብቻ 38 ጨዋታዎችን መርቷል ።
- ማሰታውቂያ -
ባምላክ ተሰማ ከመራቸው 38 ጨዋታዎች ሁለቱ የፍፃሜ ጨዋታዎች ሲሆኑ በአስገራሚ ሁኔታ ያሁኑ የፍፃሜ ተፈላሚ አል አህሊ በሁለቱም ሽንፈትን አስትናግዷል ።
በተጨማሪም በአህጉሪቱ ታላቁ የክለቦች ውድድር ላይ የሞሮኮውን ዋይዳድ ከዚህ ቀደም ለ4 ያህል ጊዜያት ያጫወተ ሲሆን አል አህሊን ደግሞ በአጠቃላይ ለ10 ጨዋታዎች መርቷል ።
በተያያዘም በግብፅ ካይሮ የሚደረገው የመጀመሪያ ጨዋታን እንዲመሩም ሊብያዊው ዳኛ ኢብራሂም ሙታዝ ተመድበዋል ።