የደቡቡ ተወካይ ክለብ ሀዋሳ ከተማ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የቀድሞ ተጫዋቹን ሙሉጌታ ምህረትንበዋና አሰልጣኝነት ሲቀጥር ለረጅም ዓመታት በሥራ አስኪያጅነት ክለቡን ሲመሩ የነበሩት አቶ ጠሀ አህመድ ጋር መለያየታቸው ተገልጿል ::
ክለቡን ለበርካታ አመታት የመሩት አቶ ጠሀ አህመድ በትናንትናው እለት የስንበት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ሀትሪክ ከቅርብ ምንጮች ለማወቅ ስትችል ምክንያቱ ግን በግልፅ አልተነገረም :: የክለቡ ፀሀፊ የነበሩት አቶ አንዱአለም አረጋ በጊዚያዊ ስራ አስኪያጅነት ተተክተው እሚያገለግሉ ይሆናል
ሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ በመጪው ቀናት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ::