የቀድሞው የሃድያ ሆሳአና፣መቐለ 70 አንደርታ፣አዳማ ከተማ ተጨዋች ዱላ ሙላቱ በሳምሶን ነስሩ በሚመራው ሰርነስ ሶከር ኤጀንሲ አማካኝነት የተገኘውን የሙከራ ዕድል ለመጠቀም ወደ ዱባይ አቅንትዋል።
ባሳለፍነው አመት ከአዳማ ከተማ ጋር ያሳለፈው ዱላ ሙላቱ በዱባይ ቆይታው በሳይፐርስ አና ቱርኪ ክለቦች (አናላይስፖር) ላይ የሙከራ ጊዜ ሚያሳልፍ ይሆናል።
በ2007 ሃድያ ሆሳአና ወደ ፕሪምየር ሊጉ አንዲያድግ ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው ተጨዋቾች መሃል በቀዳሚነት ሚጠቀሰው ዱላ ሙላቱ፤ በ2008 ክለቡ ሃድያ ሆሳአና በፕሪምየር ሊጉ ጥሩ የውድድር ዓመት ባያሳልፍም በግሉ ጥሩ መንቀሳቀስ ችልዋል።
- ማሰታውቂያ -
ከዚህ ቀደም ሎዛ አበራ በማልታው ክለብ ቢርኪርካራ የሙከራ አድል አንድታገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የደረጉት ሰርነስ ሶከር ኤጀንሲ በቀጣይነትም ተሰጥኦ ያላቸው የኢትዮጵያ ተጨዋቾች የውጭ አድል ሚያገኙበትን መንገድ አየከፈተ ይገኛል።