ውበቱ ኣባተን በኣሰልጣኝነት ከቆጠሩ በኃላ በጥሩ መነቃቃት ሚገኙት ፋሲሎች የደደቢቱን ሽመክት ጉግሳን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረም ችለዋል።የቀድሞው የሃዋሳ እና የወላይታ ድቻ ኣማካይ ሽመክት ከመስመር እየተነሳ የሚያደርጋቸው የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ለተቃራኒ ቡድን ፈታኝ ናቸው።
ደደቢትን በ2006 ዓ/ም የተቀላቀለው ሽመክት ኣምስት ዓመታትን ከሰማያውዮቹ ጋር ማሳለፍ ችሏል፤ከቡድኑ ጋርም የኣፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ መጫወት የቻለ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመትም በግሉ ጥሩ ግዜ ማሳለፍ ችሏል።በተመሳሳይ ዜና ፋሲል ከተማ የግራ መስመር ተከላካዩን ኣምሳሉ ጥላሁንን ውል ለሁለት ዓመት ማራዘሙን ኣሳውቅዋል።