አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ከጅማ አባጅፋር ጋር የነበረውን ውል ቀዷል

ከ7ወራት በላይ ደመወዝ አልተከፈለኝም የፊርማ ግማሽ ክፍያም አልተሰጠኝም በሚል ራሱን ከአሰልጣኝነት ያገለለው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውና ጅማ አባጅፋር በመጨረሻም ተለያይተዋል።

ባለፈው ዓርብ የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ሰዎችና የክለቡ አመራሮች ከአሰልጣኙ ጳውሎስ ጋር ተደራድረው አሰልጣኙ ” ብዙ ገንዘብ ቀርቶብኛል ግን ጅብ አይደለሁም ጨዋ ቤተሰብ ያሳደገኝ ነኝ የ2 ወር ደመወዜን አስገቡ” ብሎ በመስማማቱ የክለቡን ሰዎች እፎይ አስብሏል። ፌዴሬሽን ሄደው ውሉ ተቀዶ የአዲሱ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማርያምም ውል ህጋዊ ሊሆን ችሏል። ጅማ አባጅፋር በአዲሱ አሰልጣኝ ጸጋዬ እየተመራ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የባህርዳር ስታዲየም ጨዋታ በሱራፌል አወል ብቸኛ ግብ የመጀመሪይውን ድል አስመዝግቧል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *