መነሻ ገጽ FIFA ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርት ሆነው ተሾሙ
FIFAዜናዎች

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርት ሆነው ተሾሙ

አጋራ
አጋራ

የካፍ ኤሊት ኢንስራትክተር እና የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርት ሆነው ተሹመዋል።

ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ በኤሊት ኢንስራክተርነት ፣ በአፍሪካ ዋንጫ እና መሰል ትልልቅ ውድድሮች በቴክኒክ ጥናት ቡድን አባልነት እና አሰልጣኝነት በተጨማሪም በኤዥያ እና የመን እግር ኳስ ላይ ያላቸው የስራ ልምድ ለቦታው ተመራጭ ያደረጋቸው ሲሆን ፊፋ ለቴክኒክ ኤክስፐርትነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የ2 ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርት ሆነዋል። በዚህም በፊፋ በዚህ ዘርፍ የተመረጡ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ኢንስራትክተር ሆነዋል።

በፊፋ የቴክኒክ ኤክስፐርትነት ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል በኤሊት የእግር ኳስ አሰልጣኝነት ፣ በወጣቶች እግር ኳስ ፣ በግራስ ሩት ፣ ለቴክኒክ ዳይሬክተሮች ፣ ለኢንስትራክተሮች እና ከእግር ኳስ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ጉዳዮች ዙርያ ኮርሶች ማዘጋጀት ፤ ለአባል ሀገራት እና አህጉራዊ ኮንፌዴሬሽኖች በእግር ኳስ ልማት ዙርያ የቴክኒክ ማማከር ፤ የአባል ሀገራት የእግር ኳስ ልማት ፕሮግራሞች እና ተግባራትን መከታተል ፤ አዲሱ የፊፋ ቴክኒክ ልማት ፕሮግራም ዝግጅት እና አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ መሳተፍ እንዲሁም ሌሎች በፊፋ የቴክኒክ ልማት መምሪያ ስር የሚሰጣቸው ተግባራትን መከወን ይጠቀሳሉ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በፊፋ በተሰጣቸው የስራ ኃላፊነት የተሰማውን ደስታ እየገለፀ በአዲሱ ስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...