የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮኖቹ ፋሲል ከነማ ቴሌቶን አዘጋጁ።

የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን 4 ጨዋታዎች እየቀሯቸው የዋንጫው አሸናፊ መሆናቸውን ያረጋገጡት አፄዎቹ በመጭው ማክሰኞ ግንቦት 17 ‘ስፖርት ለኢትዮጵያ ህብረት’ በሚል መሪ ቃል ቴሌቶን ማዘጋጀታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የቴሌቶን መርሀግብሩ በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ሲካሄድ የዋንጫ አሰጣጥ እና ክለቡን በገቢ የማጠናከር መርሀግብር እንደሚኖር ታውቋል።