ፋሲል ከነማ ዋንጫውን እሚረከብበት ቀን ታውቋል

በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በሚኖረው ጨዋታ በማሽነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ቢያረጋግጥም ዋንጫውን የሚረከበው ግንቦት 8/ 2013 መሆኑ ታውቋል።

ከሊግ ካምፓኒው በተገኘ መረጃ የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው ጨዋታ ሊሽነፍ የሚችልበት እድል መኖሩና አስቀድሞ ጨዋታውን የሚያደርገው ኢትዮዽያ ቡና ነጥብ ጥሎ ፋሲል ከነማ ዋንጫ መውስዱን ቢያረጋግጥም ለሽልማት የዝግጅት ጊዜ ስለሚያጥር የዋንጫ መስጠት ስነስርአቱ እንደማይካሄድ ታውቋል። በ23ኛው ሳምንት ጨዋታዎችም ክለቡ ስለሚያርፍ በ24ኛው ሳምንት እሁድ ግንቦት 8/2013 ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ዋንጫው እንደሚሰጠው ታውቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport