18ቱ ዳኞች ኮቪድ 19 የለባችሁም ተባሉ

በድሬዳዋ እየተካሄደ ባለው የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ በኮቪድ 19 ከተጠረጠሩ 18 አርቢትሮች 17ቱ ነጻ መሆናቸው ታውቋል።

በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤቱን ባለመቀበል በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የድጋሚ ምርመራ ካደረጉ 11 ረዳት ዳኞችና 7 የመሃል ዳኞች መሃል ኮቪድ 19 እንዳለበትና ራሱን እንዲያገል የተነገረው ፌዴራል አርቢትር አሽብር ሰቦቃ ብቻ መሆኑ ታውቋል።

ይሄ የምርመራን ወጤት ተከትሎ የኢትዮዽያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታን በመሃል ዳኝነት እንዲመሩ የተደረጉት የመሃል ዳኛው በአምላክ ተሰማና 4ኛ ዳኛው ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ባሉበት ሲቀጥሉ የረዳቶች ለውጥ የተደረገ ሲሆን ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞች የሆኑት ተመስገን ሳሙኤልና ክንዴ ሙሴ መመደባቸው ታውቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport