አዳማ ከነማ

አዳማ ከነማ

adama-city-football-club-logo-12.png

አዳማ ከነማ ስፖርት  ክለብ
ስታድየም አዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም

የክለቡ የወቅቱ አሰልጣኝ፡– ተገኔ ነጋሽ
/አሰልጣኝ –  አስቻለው
የህክምና ባለሙያ – ዮሐንስ ጌታቸው

 

አዳማ ከነማ በ 1983 ዓ/ም የተመሰረተና በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የሚሳተፍ ክለብ ነው፡፡ ከ 1992 ጀምሮ የተቀላቀለ ሲሆን በ 2000 ዓ/ም ሁለተኛ የወጣበት ደረጃ የተሻለው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ምስረታ

 

የአዳማ ከነማ ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1984 ዓ/ም ነው፡፡ በወቅቱ በአዳማ ከተማ ባሉ 20 ቀበሌዎች መካከል ውድድር ከተደረገ በኃላ ከየክለቡ የተሻለ ብቃት የነበራቸው ወጣቶች ይመረጡና አዳማ ከነማ ይመሰረታል፡፡ እስከ 1987 ዓ/ም በምስራቅ ሸዋ ዞን የክለቦች ሻምፒዮና ተሳተፈ፡፡ በሌሎች ውድድሮች  በ 1988 የኦሮሚያ ሊግ ሲጀመር ሊጉን ተቀላቀለ፡፡ እስከ 1991 በኦሮሚያ ሊግ  የተሳተፈ ሲሆን በአራተኛው የውድድር ዘመኑ የሊጉ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ በዚህም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ በተደረገ ውድድር ተሳትፎ ውድድር ተሳትፎ ሊጉን ተቀላቀለ፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 

አዳማ ከነማ የአትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በተቀላቀለበት 1992 ከነበሩት 12 ክለቦች 11ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ፡፡ ይሁንና በቀጣይ አመት የተሳታፊዎቹ ክለቦች ብዛት ወደ 14 አድጎ ስለነበር ወደ ብሔራዊ ሊግ ሳይወርድ ቀርቷል፡፡ በቀጣዬቹ ሁለት አመታት ደረጃውን ለማሻሻል ከ14 ክለቦች 7ኛ ሆኖ አጠናቀቀ፡፡ በ 1995 አራተኛ  ደረጃን አገኘ፡፡

አዳማ የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው በ 2000 ዓ/ም ነበር፡፡ ከሻምፒዮኑ ቅ/ጊዮርጊስ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ያገኘበት ውጤት እስካሁንም ምርጥ ውጤቱ ሆኗል፡፡ በወቅቱ የቡድኑ አሰልጣኝ የነበረው ውበቱ አባተ የሊጉ ታታሪ አሰልጣኝ ተብሎ ተሸልሟል፡፡

በ 2001 አዳማ ከነማ ባልተጠበቀ ሁኔታ በርካታ ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት አጠናቀቀ፡፡ ካደረጋቸው 30 ጨዋታዎች ከግማሽ በላይ 18 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተለያየ በስድስቱ አሸንፎ በስድስቱ ተሸንፎ በ36 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡ በቀጣዩ የ 2002 የውድድር ዘመን አዳማ ከአሰልጣኝ ጀምሮ ለውጦችን አድርጓል፡፡ ወደ ደደቢት በሄደው ውበቱ አባተ ምትክ ዘላለም ሽፈራውን አሰልጣኙ በማድረግ ወሰደ።ዘላለም የደቡብ ፖሊስ ተጫዋቾችን ይዞ ነበር ወደ አዳማ የተጓዘው፡፡ የመጀመሪያውን ዙርም ከደደቢትና ቅ/ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡