​የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ቤስት ስፖርት መፅሔት በእዚህ ወር እትሟ 

የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ቤስት ስፖርት መፅሔት በእዚህ ወር እትሟ በሀገር ውስጥ እና በተለያዮ ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ዘገባዎች ላይ በማተኮር እንደቀድሞ ሁሉ እርስዎን በንባብ ለማርካትና ለማስደሰት መሰናዶዋን አጠናቃለች፡፡ መፅሔቷ ነገ ቅዳሜም በገበያ ላይም ትውላለች፡፡


ቤስት ስፖርት በሀገር ውስጥ የነገው እትም በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ይጫወት ከነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና አሁን በድጋሚ ደደቢትን ከተቀላቀለው ጌታነህ ከበደ ጋር ሰፊ ቆይታ አድርጓል፡፡

ከውጪ ሀገር አርሰናልን አስመልክቶ የቡድኑ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል እያሳለፈው ስላለው ምርጡ ሲዝን ይናገራል፡፡

ስለ ሊቨርፑል የየርገን ክሎፕ የአንድ ዓመት የአንፊልድ ቆይታን በሚመለከት ሰፊ ዘገባ ቀርቧል፡፡

የቼልሲውን ዳቪድ ሉዊስ እና የማንቸስተር ዩናይትዱን ማርከስ ራሽፎርድን በሚመለከት እና ሌሎችም ሊወዱት የሚችሉት ጣፋጭና አዝናኝ ዘገባዎችንም ይዛሎት መጥታለች እና እንዳታመልጦት፡፡
የቤስት ስፖርት መፅሔት የነገው እትምም የፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

You may have missed