​የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ!!!


6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ቀጥሎ ስምንት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።   

በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፥ 9 ሰዓት ላይ ደደቢት ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፤ 11 ስአት ከ30 ላይ ደግሞ መከላከያ ከጅማ አባቡና ይገናኛሉ።

በክልል ስታዲየሞች ወላይታ ዲቻ ሶዶ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናግዳል። ኢትዮጵያ ቡና ባሳለፍነው ቅዳሜ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 በማሸነፍ የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥቡን በሊጉ ማግኘቱ ይታወሳል። በአንጻሩ ወላይታ ዲቻ በሜዳው ከድሬዳዋ ከተማ ጋር አቻ ወጥቷል።

ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ደረጃቸውን ለማሻሻል ከሚደረገው ፉክክር ጎን ለጎን ከመሪ ክለቦች ላለመራቅ የሚደረግም ይሆናል።

አርባምንጭ በሜዳው ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚጫወት ሲሆን፥ ሁለቱም ክለቦች በደረጃው ሰንጠረዥ በእኩል አምስት ነጥብ 10ኛ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ከአምስት ጨዋታ መካከልም 1 ጨዋታ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት።

በሌላ ጨዋታ የሊጉ ጠንካራ ቡድኖችን ነጥብ ያስጣለው ፋሲል ከተማ ጎንደር ላይ ሀዋሳ ከተማን ያስተናግዳል።

አዳማ ከወልዲያ፣ ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ድሬዳዋ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እሁድ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ድሬዳዋ ከንግድ ባንክ የሚያደርገው ጨዋታ 10 ሰዓት ላይ የሚጀመር ሲሆን፥ ሌሎች ጨዋታዎች 9 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል። ሊጉን ከአምስት ጨዋታ 10 ነጥብ መሰብሰብ የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲመራ ሲዳማ ቡና በዘጠኝ፣ ደደቢትና አዳማ በ8ነጥብ ተከታዩን ስፍራ ይዘዋል።

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ጌታነህ በአምስት ሲመራ፤ ያቡን ሳላዲን እና አዳነ ግርማ በሶስት ግብ ይከተላሉ።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook