በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲቀናው መከላከያ በአቻ ውጤት ተለያይቷል 

አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል

 

8 ስአት ላይ ውድድሩ ሲጀመር በምድብ 1 መከላከያ ከክልል ከተጋበዘው ጅማ አባቡና ጋር ተጫውቶ 0 ለ 0 አቻ ተለያይቷል።

በዚሁ ምድብ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ አበቡበከር ሳኒ እና ራምኬል ሎክ ሁለት ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ብቸኛዋን ግብ  አዲስ ነጋሽ ነው በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረው።

በዚህም መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ምድቡን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምሯል።

 

 

ውድድሩ በነገው እለት ሲቀጥል በ8:00 አትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አ/አ ከተማ  በ 10:00 ደደቢት ከ አዳማ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

ምድብ ሀ

ማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2009

08፡00 መከላከያ ከ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ

10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ቡና

ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2009

08፡00 ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ ጅማ አባ ቡና

10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ

ምድብ ለ

እሁድ ጥቅምት 13 ቀን 2009

08፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዲስ አበባ ከተማ

10፡00 ደደቢት ከ አዳማ ከተማ

ረቡእ ጥቅምት 16 ቀን 2009

08፡00 አዲስ አበባ ከተማ ከ ደደቢት

10፡00 አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

እሁድ ጥቅምት 20 ቀን 2009

08፡00 አዳማ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ

10፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ደደቢት

 

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook