​<<ለሻምፒዮናነት ያ ካልተሳካ የደረጃ ተፎካካሪ ለመሆን ነውእየተጫወትን ያለነው>>አዲስ ግደይ /ሲዳማ ቡና/


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ

ጥሩ ብቃታቸውን እያሳዩ ከመጡ ተጨዋቾች መካከል ስሙ

ይጠቀሳል፤ የሲዳማ ቡና ክለብን በተቀላቀለበት እና በሊጉም

ገና አሁን የሁለተኛ ዓመት ልምድን እያገኘ በመጣበት ጊዜያትም

የሚያሳየው የሜዳ ላይ ብቃት የብዙዎቹን የእግር ኳስ

አፍቃሪዎች ትኩረትን እያገኘም መጥቷል፤ ይህ ተጨዋች አዲስ

ግደይም ይባላል፤ የሲዳማ ክለብ ውስጥ የ14 ቁጥር መለያን

በማጥለቅ የአጥቂው ስፍራ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ

የመጣው ይህ ተጨዋች በቀጣይ ጊዜም በእግር ኳሱ የተሻለ

ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሎም ግምት ተሰጥቶታል፤ የሲዳማ ቡና

እግር ኳስ ክለብ በደቡብ ሲቲ ካፕ ሻምፒዮና ላይ አርባ ምንጭ

ከተማን በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮና ሲሆን የውድድሩ ኮከብ

በሚል የተሸለመው አዲስ በዘንድሮ የፕሪምየር ሊግ ጅማሬ

ጨዋታዎችም ለክለቡ አበረታች እንቅስቃሴ በማሳየት ጥሩ

ጅማሬውን እያሳየ ይገኛል፤ ለሲዳማ ቡና በሊጉ ጅማሬ

ጨዋታዎችም ከወዲሁ ሁለት ግብ ሊያስቆጥርም ችላል፤

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን በሊጉ የአምስት ሳምንት

ጨዋታዎች 3 ጨዋታዎችን በማሸነፍ እና ሁለት ጨዋታዎችን

በመሸነፍ 9 ነጥብን ይዞ 10 ነጥብን ከያዘው ከቅዱስ ጊዮርጊስ

በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የክለቡን የሊጉን

ጉዞና እሁድ ዕለት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስላደረጉት ጨዋታ

እንደዚሁም ስለራሱ አቋም በሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ

ጠይቀነው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡


የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስላደረጋችሁት እና ሸንፈትን

ስላስተናገዳችሁበት ጨዋታ

የኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረግነው ጨዋታ በጣም ከባድ እና

ጥሩም ነበር፡፡ ሁለታችንም ጥሩም ተንቀሳቅሰናል፤ እነሱ

በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ውስጥ ያገኙትን አጋጣሚ

ስለተጠቀሙም ጎል ሊያስቆጥሩብንና በመጨረሻ ሰአቶታች

ደግሞ የያዙትን ውጤት አስጠብቀው ለመውጣት ጥረት

ስላደረጉ በእዚህ መልኩ ሊያሸንፉ ችለዋል፡፡

ለሽንፈታችሁ የእናንተ ድክመትና ክፍተት ምንድን ነበር

የሲዳማ ቡና የቅዳሜ ጨዋታ ላይ ለሽንፈቱ እንደ ክፍተት ወይም

ድክመት የምጠቅሰው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ እንደ ሁለተኛ

አጋማሽ ጥሩ ልንቀሳቀስ አለመቻላችን ነው ይህንን ማድረግ

ብንችል ውጤቱን መቀየር እንችል ነበር፡፡ የመሃል ክፍሉ ላይ

ክፍተት ነበረብን እነሱ ደግሞ መሃል ላይ ኳሱን ይቆጣጠሩ

ነበርና የሁለተኛ አጋማሽ ላይ ወደ ጥሩነት ስለመጣን ውጤቱን

ልናጠበው ችለናል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን በቀጣይነት

ትፋለማላችሁ ምን ውጤት ትጠብቃለህ?

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድንን ይርጋዓለም ላይ በሚደረገው ጨዋታ

ለማሸነፍ በሁሉም መልኩ ዝግጁ ነን፡፡ ያንንልል የቻልኩትም

ከቡናው ሽንፈት በኋላ ያለን የራስ መተማመን ስሜት ጥሩ

ስለሆነ ነው ተነሳሽነታችንም መልካም ነው፡፡

የሲዳማ ቡና የዘንድሮው የሊጉ ዕቅድ

የሲዳማ ቡና ክለብ እንደ ቦርድም እንደተጨዋቾችም ፍላጎት

እያሰበ ያለው ሊጉን በሻምፒዮንነት ማጠናቀቅና ያ ካልተሳካ

ደግሞ ከ1-3ኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ሆና ለማጠናቀቅ ነው ያንን

ውጤት ለማምጣትም ነው እየተዘጋጀን ያለነው፡፡

ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ሲጫወት ስለነበረክ አቋም

የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስንጫወት ስለነበረኝ አቋም ስለራሴ

እንዲህ ነበርኩ ብዬ መናገር አልችልም ሰዎች ናቸው ስለእኔ

ሊነግሩኝ የሚገባው ያም ሆኖ ግን በጨዋታው ላይ አሰልጣኜ

በዛዘኝ መልኩ የአቅሜን ሙሉ ለሙሉ አውጥቼ ባልንቀሳቀስም

ጥሩ ነገር እንደነበረኝ ተመልክቻለሁ፡፡ ወደፊት ደግሞ ለክለቤ

ብዙ ጠቃሚ ብቃቴን እንደማሳይም እርግጠኛ ነኝ፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን በገጠማችሁበት ጨዋታ በምን መልኩ ተሸነፍን

ትላለህ

የኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረግነው ጨዋታ እኛ ሸንፈትን

ያስተናገድነው በሰራናቸው ጥቃቅን ስህተቶች እንጂ ሌላ

ምክንያቶችን ለምሳሌ ዳኛ ተጽዕኖ ፈጥሮብናል በሚል ጠቅሼ

መናገርን አልፈልግም፡፡ ዳኛ ፔናሊቲ አምኖ ከሰጠ ሰጠ ማለት

ነው፤ ያንን ልትቀበለው የግድ ይልሃል፡፡ በእንቅስቃሴ ላይ ደግሞ

አንድ አንዴ ዳኞች ሲወስኑ በደጋፊ ተፅዕኖ ውስጥ ገብተውም

ሊሆን ይችላል፡፡ ዳኞች ቅጣቶችን ሊሰጡም ላይሰጡም

ይችላል፤ ያንን እንደአመጣጡ ነው ልትቀበል የሚገባውና እኛ

የተሸነፍነው በራሣችን ድክመት እና ቡና በመጀመሪያው አጋማሽ

ጥሩ ስለነበር እንጂ በሌላ ነገር አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ስላለው ፉክክር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዚህ አመት ፉክክር የተወዳዳሪዎች

ቁጥር ከመጨመሩም በነጥብ ከመቀራረቡም አንፃር በጣም

ይለያል እንዲህ ያለ ፉክክርም ሲኖርም ነው የእግር ኳሱ

ሊያድግ የሚችለው፡፡ ስለዚህም ሁሉም ይህን ጅማሬ

ሊቀጥልበት ይገባል፡፡ የሊጉ ውድድር ላይ ብዙ ቡድኖች

በሜዳቸው ነጥብ አይጥሉም፤ አሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ እየመራ

ነው፤ እኛ እየተከተልነው ነውና በቀጣይነት ፉክክሩ በድምቀት

ይቀጥላል እኛም ከቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ለመረከብ

ተዘጋጅተናል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስትጫወቱ ስለነበረው ድባብ

የኢትዮጵያ ቡና ጋር ዘንድሮ ብንሸነፍም አምና ተጫውተን

አሸንፈናል፤ ያኔም ጎል ማግባት ችያለሁ፤ ያን እለት የነበረውን

ድባብ አስታውሰዋለሁ፡፡ የአሁኑ ድባብ ደግሞ ይለያል፡፡ በጣም

ያምር ነበር፤ የቡና ደጋፊዎች በጣም ደስ ይላሉ ተቃራኒ ሆነ

እንኳን ስትጫወት የምትቀናባቸው ደጋፊዎች ናቸው እስከ

መጨረሻ ሰዓት ድረስ ነው የሚደግፏቸውና ለእዚያም ነው

አሸናፊ የሆኑት፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

You may have missed